ስለ ድረ ገጹ

እንኳን ወደ ነገደ ጎበዜ ቤተ መዝገብ  በደህና መጡ

  • በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ ተሰባስበው የቀረቡት ጽሁፎች፣ በአብዝኛው ከነገደ የግል ማህደር የተገኙ ናቸው። ጽሁፎቹም አንዳንዶቹ በስሙ የተፈረሙ፣ አንዳንዶቹ በብእር ስም የወጡ ሌሎቹ ደግሞ ያልተፈረሙባቸው ይገኙበታል።
  • የጽሁፎቹ አርእስትና ቀን ፣እንዲሁም ጽሁፉ የወጣበትን መጽሄት፣ ጋዜጣ፣ ድርጅት፣ ማህበር ወዘተርፈ፣ ዝርዝሩን መዝግቦ ስላስቀመጠው ፣ ጽሁፎቹን ማሰባሰብና ማቀናጀት ቀላል ነበር ማለት ይቻላል።
  • ድረገጹ የተዘጋጀው በቤተሰቡ ሲሆን የቀረበውም እንደ ግል ቤተ መዝገብ/ቤተ መጽሃፍት በዋናነት ለልጆቹና ለልጅ ልጆቹ፣ የአባታቸውን፣ የአያታቸውን ታሪክ እንዲያውቁት ለማስተላለፍ የታቀደ ነው።
  • በተጨማሪ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች ለሚያደርጉት ጥናት፣ምርምርም ሆነ ትንተና እንደ መረጃ/ ማገናዘቢያ (reference) በተወሰነ ደርጃ አስተዋጽኦ ያደርጋል በለን ተስፋ እናደርጋለን።
  • መረጃ ማሰባሰብና ተደራሽ ማድረግ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ እውቀትን ለማዳበር ይረዳል የሚል ጽኑ እምነት አለን።
  • በዚህ ድረ ገጽ ላይ የተሰበሰበውን ሰነድ ምንጩ እስከተጠቀሰ ድረስ ለትርፍ ላልሆነ ዓላማ መጠቀም ይቻላል። ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ “ከነገደ ጎበዜ የግል መዘገብ የተገኘ - www.negedegobezie-archives.com» የሚለውን ሃረግ እንዲጨምሩ በትህትና እንጠይቃለን።
  • ይህንን ድረ ገጽ ለማዘጋጀት፣ ሰነዶችን በማፈላለግ ለረዱን በዋሽንግተን ዲሲ፣ በስዊድን፣ በጀርመን፣ በቤልጅየም፣በኢትዮጵያ ለሚገኙት ወዳጆቻችንን የልብ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።
  • አዘጋጅ-:  ጽጌረዳ ዋለልኝ (info@negedegobezie.com)

ስለ

እንኳን ወደ ነገደ ጎቤዚ ማህደር ቦታ በደህና መጡ።

Negede Gobezie

Privacy Preference Center